1 ቆሮንቶስ 2:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዐዋቂዎች መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን፤ ይሁን እንጂ የዚህን ዓለም ወይም መጨረሻቸው ጥፋት የሚሆነውን የዚህን ዓለም ገዢዎች ጥበብ አይደለም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በበሰሉ ሰዎች መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን፤ ይሁን እንጂ የዚህችን ዓለም ጥበብ ወይም የሚጠፉትን የዚህችን ዓለም ገዦች ጥበብ አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በመንፈሳዊ ሕይወት ለበሰሉት በጥበብ ቃል እንናገራለን፤ ይሁን እንጂ የምንናገረው የዚህን ዓለም ጥበብ ወይም መጨረሻቸው ጥፋት የሚሆነውን የዚህን ዓለም ገዢዎች ጥበብ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዐዋቆች ጥበብን እንነግራቸዋለን፤ ነገር ግን የዚህን ዓለም ጥበብ ወይም ያልፉ ዘንድ ያላቸውን የዚህን ዓለም ሹሞች ጥበብ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በበሰሉት መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን፥ ነገር ግን የዚችን ዓለም ጥበብ አይደለም የሚሻሩትንም የዚችን ዓለም ገዦች ጥበብ አይደለም፤ |
ይህን ደግሞ፥ መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን፥ መንፈስ በሚያስተምረን ቃል እንናገራለን እንጂ ከሰው ጥበብ በሚገኝ ቃል አይደለም።
ወንድሞች ሆይ! እኔም፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም።
ትምክህታችን ይህ ነው፦ በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ባልሆነ፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን፥ የሕሊናችን ምስክርነት ነው።
በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! ደኅና ሁኑ። ፍጹማን ሁኑ፤ ምክሬን ስሙ፤ በአንድ ልብ ሁኑ፤ በሰላም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
እንደ እነርሱ ከሆነ የማያምኑ ሰዎችን ልቦና፥ የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ አሳውሯል።
በዚህም የዚህን ዓለም አኗኗር በመከተል፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው፥ በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ እየታዘዛችሁ ትኖሩ ነበር።
እኛም በክርስቶስ ፍጹም አድርገን ሁሉንም ሰው ለማቅረብ ሁሉንም ሰው እየገሠጽንና ሁሉንም ሰው በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤
ከእናንተ ወገን የሆነ የክርስቶስ ባርያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይተጋል።
ስለዚህ የክርስቶስን የመጀመሪያ ትምህርት አልፈን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፤ እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሓና በእግዚአብሔር እምነት፥
በክርስቶስ ወደ ዘለዓለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ፥ እርሱ ራሱ ያበረታችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ያቆማችኋል፤ ይመሠርታችኋልም።