1 ቆሮንቶስ 15:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትንሣኤ ከሌለማ ለሞቱ ሰዎች ብለው የሚጠመቁት ምን እያደረጉ ነው? ሙታን ከቶ የማይነሡ ከሆነ፥ ሰዎች ለእነርሱ ብለው ለምን ይጠመቃሉ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትንሣኤ ከሌለማ ለሞቱ ሰዎች ብለው የሚጠመቁት ምን እያደረጉ ነው? ሙታን ከቶ የማይነሡ ከሆነ፣ ሰዎች ለእነርሱ ብለው ለምን ይጠመቃሉ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ የሞቱ ሰዎች የማይነሡ ከሆነ ስለ ሞቱ ሰዎች የሚጠመቁ ሁሉ ትርፋቸው ምንድን ነው? የሞቱ ሰዎች ከቶ የማይነሡ ከሆነ ሰዎች በእነርሱ ምትክ ስለምን ይጠመቃሉ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያለዚያማ ለምን ያጠምቃሉ? ሙታን እንዲነሡ አይደለምን? ሙታን የማይነሡ ከሆነስ ለምን ያጠምቃሉ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲያማ ካልሆነ፥ ስለ ሙታን የሚጠመቁ ምን ያደርጋሉ? ሙታንስ ከቶ የማይነሡ ከሆነ፥ ስለ እነርሱ የሚጠመቁ ስለ ምንድር ነው? |