1 ቆሮንቶስ 11:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትክክል የሆኑት እነማን እንደ ሆኑ ተለይተው እንዲታወቁ በመካከላችሁ መለያየት መኖሩ ግድ ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእናንተ መካከል እውነተኞቹ ተለይተው ይታወቁ ዘንድ፣ ይህ መለያየት በመካከላችሁ መኖሩ የግድ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትክክል የሆኑት እነማን እንደ ሆኑ ተለይተው እንዲታወቁ በመካከላችሁ መለያየት መኖሩ ግድ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተ የተመረጡት ወንድሞች ተለይተው እንዲታወቁ ትለያዩ ዘንድ ግድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእናንተ ዘንድ የተፈተኑት እንዲገለጡ በመካከላችሁ ወገኖች ደግሞ ሊሆኑ ግድ ነውና። |
ነገር ግን ይህን እመሰክርልሃለሁ፤ በሕጉ ያለውን በነቢያትም የተጻፉትን ሁሉ አምኜ የአባቶቼን አምላክ እነርሱ ኑፋቄ ብለው እንደሚጠሩት መንገድ አመልካለሁ፤
ሊመሰክሩ ይወዱ እንደሆነ፥ በአምልኮአችን ከሁሉ ይልቅ ሕግን በመጠንቀቅ እንደሚተጋ ወገን ፈሪሳዊ ሆኜ እንደኖርሁ ከጥንት ጀምረው አውቀውኛልና።
ወደ እናንት ስመጣ፥ እኔ እንደምፈልገው ሆናችሁ ላላገኛችሁ እችላለሁ ወይም እናንተ እንደምትፈልጉኝ ሆኜ ላታገኙኝ ትችላላችሁ ብዬ እፈራለሁ፤ ምናልባት ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኝነት፥ ሐሜት፥ ማሾክሾክ፥ ኩራት፥ ሁከትም ይኖር ይሆን ብዬ እሰጋለሁ።
አምላካችሁን ጌታ በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ትወዱት እንደሆነ ያውቅ ዘንድ አምላካችሁ ጌታ ሊፈትናችሁ ነውና፥ የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ሕልም አላሚውን አትስሙ።
ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ነገር ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ኖሮ ከእኛ ጋር በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ እንዲገለጥ ወጡ።