ካህኑም ሴቲቱን በጌታ ፊት ያቆማታል፥ የሴቲቱንም የተሠራ ጠጉር ይፈታል፥ በእጅዋም የመታሰቢያ የእህል ቁርባን የሆነውን የቅንዓት የእህል ቁርባን ያኖራል፤ ካህኑም እርግማንን የሚያመጣውን መራራ ውኃ በእጁ ይይዛል።
1 ቆሮንቶስ 11:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴት ግን ጠጉርዋን ብታስረዝም ክብር አይደለምን? ምክንያቱም ጠጉርዋ መጎናጸፊያ ሊሆን ተሰጥቶአታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴት ግን ጠጕሯን ብታስረዝም ክብሯ አይደለምን? ረዥም ጠጕር የተሰጣት መጐናጸፊያ እንዲሆናት ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴት ግን ጠጒር የተሰጣት ራሷን ልትሸፍንበት ስለ ሆነ ጠጒርዋን ብታስረዝም ለእርስዋ ክብርዋ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሴት ግን ጠጕርዋን ብታሳድግ ክብርዋ ነው፤ ለሴት ጠጕርዋ እንደ ቀጸላ ሆኖ ተሰጥቶአታልና። |
ካህኑም ሴቲቱን በጌታ ፊት ያቆማታል፥ የሴቲቱንም የተሠራ ጠጉር ይፈታል፥ በእጅዋም የመታሰቢያ የእህል ቁርባን የሆነውን የቅንዓት የእህል ቁርባን ያኖራል፤ ካህኑም እርግማንን የሚያመጣውን መራራ ውኃ በእጁ ይይዛል።