1 ቆሮንቶስ 11:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴት ከወንድ እንደ ሆነች ሁሉ ወንድ ደግሞ ከሴት የሚገኝ ነውና፤ ነገር ግን ሁሉም ከእግዚአብሔር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴት ከወንድ እንደ ተገኘች ሁሉ፣ ወንድም ከሴት ይወለዳልና፤ ነገር ግን የሁሉም መገኛ እግዚአብሔር ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴት ከወንድ እንደ ተገኘች እንዲሁም ወንድ የሚወለደው ከሴት ነው፤ ነገር ግን ወንድም ሆነ ሴት ሌላውም ነገር ሁሉ የሚገኘው ከእግዚአብሔር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴት ከወንድ እንደ ተገኘች እንዲሁ ወንድ ከሴት ተገኘ፤ ነገር ግን ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴት ከወንድ እንደ ሆነች እንዲሁ ወንድ ደግሞ በሴት ነውና፤ ሁሉም ከእግዚአብሔር ነው። |
ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ እግዚአብሔር አብ አለን፤ እንዲሁም ነገር ሁሉ በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።