1 ቆሮንቶስ 10:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ በአብዛኞቹ ደስ አልተሰኘም፤ እነርሱ ምድረ በዳ ወድቀው ቀርተዋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ እግዚአብሔር በብዙዎቹ ደስ ስላልተሠኘ በበረሓ ወድቀው ቀሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ሆኖ እግዚአብሔር በአብዛኞቹ አልተደሰተም፤ ስለዚህ ሬሳቸው በበረሓ ወድቆ ቀረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ በሁሉም ደስ አላለውም፤ ብዙዎቹ በምድረ በዳ ወድቀዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ በሚበዙት ደስ አላለውም፥ በምድረ በዳ ወድቀዋልና። |
በግብጽ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግሁትን ክብሬንና ተአምራቴን ያዩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ እኔን ስለ ተፈታተኑኝ፥ ድምፄንም ስላልሰሙ፥
የዘሬድንም ፈፋ እስከ ተሻገርንበት ድረስ፥ ጌታ እንደ ማለባቸው የጦረኞች ትውልድ ሁሉ ከሰፈሩ መካከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃዴስ በርኔ የተጓዝንበት ዘመን ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነ።
ነገር ግን ሁሉን ነገር አንድ ጊዜ ያወቃችሁትን እናንተን፥ ጌታ ከግብጽ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።