1 ቆሮንቶስ 10:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ምን እላለሁ? ለጣዖት የተሠዋ የሚረባ ነገር ነው? ወይስ ጣዖት የሚረባ ነገር ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ፣ ለጣዖት የተሠዋ ነገርም ሆነ ጣዖቱ ራሱ ዋጋ ያለው ነገር ነው ማለቴ ነውን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ ይህን ስል ለጣዖት የተሠዋ ሥጋ የሚረባ ነገር ነው ማለቴ ነውን? ወይስ ጣዖት የሚረባ ነገር ነው ማለቴ ነውን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ምን እንላለን? ለጣዖታት የሚሠዋ መሥዋዕት ከንቱ ነው፤ ጣዖቶቻቸውም ከንቱ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ምን እላለሁ? ለጣዖት የተሠዋ ምናምን ነው እላለሁን? ወይስ ጣዖት ምናምን እንዲሆን እላለሁን? |
ይህም ጳውሎስ ‘በእጅ የተሠሩቱ አማልክት አይደሉም፤’ ብሎ፥ በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን ከጥቂት ክፍል በቀር በእስያ ሁሉ ብዙ ሕዝብን እንደ አስረዳና እንደ አሳተ አይታችኋል፤ ሰምታችሁማል።
ትንቢት የመናገር ስጦታ ቢኖረኝ፥ ምስጢርን ሁሉ ባውቅ፥ ዕውቀትን ሁሉ ብረዳ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።
በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ! ይህ እናንተ ግድ ስላላችሁኝ የሆነ ነው። እኔ ከምንም የማልቆጠር ብሆን እንኳን፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አላንስምና፥ በእርግጥም እናንተ ስለ እኔ መናገር ይገባችሁ ነበር።