1 ዜና መዋዕል 8:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ የኤሁድ ልጆች ናቸው፤ እነዚህ በጌባ የሚቀመጡ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ናቸው፤ እነርሱም ወደ መናሐትም ተማረኩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጌባዕ ይኖሩ የነበሩትና በኋላም በምርኮ ወደ መናሐት የተወሰዱት የኤሁድ ዘሮች እነዚህ ናቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኤሁድ ዘሮች ናዕማን፥ አሒያና ጌራ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እነርሱም በጌባዕ ይኖሩ ለነበሩት በኋላ ግን ከዚያ ተባረው ወደ ማናሐት ሄደው በዚያ ለኖሩ ቤተሰቦች አለቆች ነበሩ፤ ወደዚያም የመራቸው የዑዛና የአሒሑድ አባት ጌራ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ የኤሁድ ልጆች ናቸው፤ እነዚህ በጌባ የሚቀመጡ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ናቸው፤ ወደ መነሐትም ተማረኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህም የኤሁድ ልጆች ናቸው፤ እነዚህ በጌባ የሚቀመጡ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ናቸው፤ ወደ መናሐትም ተማረኩ፤ |
እንዲሁም ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማሪያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማሪያዋን፥ ዓኖቶትንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።