1 ዜና መዋዕል 6:78 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ከሮቤልም ነገድ በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል በምድረ በዳ ያለችው ቦሶርና መሰማሪያዋ፥ ያሳና መሰማሪያዋ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ከኢያሪኮ በስተምሥራቅ ከሚገኘው ከሮቤል ነገድ፣ በምድረ በዳ የሚገኘውን ቦሶርን፣ ያሀጽ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ፥ ከኢያሪኮ ማዶ ባለው በሮቤል ግዛት በከፍተኛ ሜዳ ላይ የምትገኘው ቤጼር፥ ያህጻ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሮቤልም ነገድ በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል በምድረ በዳ ያለችው ቦሶርና መሰማሪያዋ፥ ያሶንና መሰማሪያዋ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሮቤልም ነገድ በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል በምድረ በዳ ያለችው ቦሶርና መሰማርያዋ፥ ያሳና መሰማሪያዋ፥ |
በዮርዳኖስም ማዶ ከኢያሪኮ ወደ ምሥራቅ ከሮቤል ነገድ በምድረ በዳው በደልዳላው ስፍራ ቦሶርን፥ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ራሞትን፥ ከምናሴም ነገድ በባሳን ጎላንን ለዩ።