1 ዜና መዋዕል 6:63 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሜራሪ ልጆች በየወገናቸው ከሮቤል ነገድ፥ ከጋድም ነገድ፥ ከዛብሎንም ነገድ፥ ዐሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተሰጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሜራሪ ዘሮች በየጐሣቸው ከሮቤል፣ ከጋድና ከዛብሎን ድርሻ ላይ ዐሥራ ሁለት ከተሞች ተመደቡላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ለመራሪ ጐሣ በየወገናቸው ከሮቤል፥ ከጋድና ከዛብሎን ግዛቶች በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተመድበው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሜራሪም ልጆች በየወገናቸው ከሮቤል ነገድ፥ ከጋድም ነገድ፥ ከዛብሎንም ነገድ፥ ዐሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሜራሪ ልጆች በየወገናቸው ከሮቤል ነገድ፥ ከጋድም ነገድ፥ ከዛብሎንም ነገድ፥ ዐሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተሰጡ። |
ለጌድሶንም ልጆች በየወገናቸው ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ፥ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጡ።
ከተሞቹም ለሮቤል ነገድ በምድረ በዳ በደልዳላ ስፍራ ያለ ቤጼር፥ ለጋድም ነገድ በገለዓድ ያለ ራሞት፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ያለ ጎላን ነበሩ።