1 ዜና መዋዕል 6:48 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ቤት ማደሪያ አገልግሎት ሁሉ ተሰጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌዋውያን ወንድሞቻቸው ግን የእግዚአብሔርን ቤት የማደሪያ ድንኳን ተግባር እንዲያከናውኑ ተመድበው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌዋውያን የሆኑ የእነርሱ ወገኖችም በእግዚአብሔር ቤት ሌላውን ተግባር ሁሉ ያከናውኑ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን እንደ እየባቶቻቸው ቤቶች ለእግዚአብሔር ቤት ሥራ አገልግሎት ሁሉ ተሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ቤት ማደሪያ አገልግሎት ሁሉ ተሰጡ። |
አሮንና ልጆቹ ግን የእግዚአሔር ባርያ ሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ለቅድስተ ቅዱሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስራኤልም ለማስተስረይ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕጣኑም መሠዊያ ላይ ያጥኑ ነበር።
ለጌድሶንም ልጆች በየወገናቸው ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ፥ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጡ።