በሳኦልም ዘመን ከአጋራውያን ጋር ተዋጉ፥ እነርሱም በእጃቸው ተመትተው ወደቁ፤ በገለዓድ ምሥራቅ በኩል ባለው አገር ሁሉ በድንኳኖቻቸው ተቀመጡ።
1 ዜና መዋዕል 5:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሮቤልና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ፥ ጽኑዓን፥ ጋሻና ሰይፍ የሚይዙ፥ ቀስተኞችም፥ የውግያ ስልት የሚያውቁ ተዋጊዎችም፥ አርባ አራት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሮቤል፣ የጋድና የምናሴ ነገድ እኩሌታ አርባ አራት ሺሕ ሰባት መቶ ስድሳ ብቁ የጦር ሰዎች ነበሯቸው። እነርሱም ጋሻ መያዝ፣ ሰይፍ መምዘዝና ቀስት መሳብ የሚችሉ ጠንካራና በውጊያ የሠለጠኑ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሮቤል፥ የጋድና በስተ ምሥራቅ የሚገኘው የምናሴ ነገድ እኩሌታ በጋሻና በሰይፍ እንዲሁም በቀስት ውጊያ በደንብ የሠለጠኑ አርባ አራት ሺህ ሰባት መቶ ሥልሳ ወታደሮች ነበሩአቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሮቤልና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ፥ ጽኑዓን ጋሻና ሰይፍ የሚይዙ፥ ቀስተኞችም፥ ሰልፍ የሚያውቁ ሰልፈኞችም፥ አርባ አራት ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሮቤልና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኵሌታ፥ ጽኑዓን፥ ጋሻና ሰይፍ የሚይዙ፥ ቀስተኞችም፥ ሰልፍ የሚያውቁ ሰልፈኞችም፥ አርባ አራት ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ነበሩ። |
በሳኦልም ዘመን ከአጋራውያን ጋር ተዋጉ፥ እነርሱም በእጃቸው ተመትተው ወደቁ፤ በገለዓድ ምሥራቅ በኩል ባለው አገር ሁሉ በድንኳኖቻቸው ተቀመጡ።
ሙሴም ለጋድና ለሮቤል ልጆች ለዮሴፍም ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ፥ የአሞራውያንን ንጉሥ የሴዎንን ግዛት የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ግዛት፥ ምድሪቱንና ከተሞቹን በከተሞቹም ዙሪያ ያሉትን ግዛቶች ሰጣቸው።