ለሴቲቱም አላት፥ “በእርግዝናሽ ወራት ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፥ በጭንቅ ትወልጃለሽ፥ ይህም ሁሉ ሆኖ ፍላጎትሽ ለባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።”
1 ዜና መዋዕል 4:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፤ እናቱም፦ “በጣር ወልጄዋለሁና” ብላ ስሙን፦ ያቤጽ ብላ ጠራችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያቤጽ ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ሰው ነበረ፤ እናቱም “በጣር የወለድሁት” ስትል ስሙን ያቤጽ አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከቤተሰቡ መካከል እጅግ የተከበረ ያዕቤጽ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበር፤ እናቱ እርሱን በወለደች ጊዜ ከባድ የምጥ ጣር ደርሶባት ስለ ነበር “ያዕቤጽ” የሚል ስም አወጣችለት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያግቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፤ እናቱም፦ በጣር ወልጄዋለሁና ብላ ስሙን፦ ያግቤጽ ብላ ጠራችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፤ እናቱም “በጣር ወልጄዋለሁና” ብላ ስሙን “ያቤጽ” ብላ ጠራችው። |
ለሴቲቱም አላት፥ “በእርግዝናሽ ወራት ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፥ በጭንቅ ትወልጃለሽ፥ ይህም ሁሉ ሆኖ ፍላጎትሽ ለባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።”
ያቤጽም፦ “እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ይሁን፤ እንዳይጎዳኝም ከክፋት ጠብቀኝ” ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና “ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን?” ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።