አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፥ እንጀራንም ወሰደ፥ የውኃ አቁማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፥ ብላቴናውንም ሰጥቶ አስወጣት፥ እርሷም ሄደች በቤርሳቤህም ምድረ በዳ ተቅበዘበዘች።
1 ዜና መዋዕል 4:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ የሰፈሩት በቤር-ሳቤህ፥ በሞላዳ፥ በሐጸርሹዓል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኖሩባቸውም ቦታዎች እነዚህ ናቸው፦ ቤርሳቤህ፣ ሞላዳ፣ ሐጻርሹዓል፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ድረስ የስምዖን ዘሮች በሚከተሉት ከተሞች ይኖሩ ነበር፦ ቤርሳቤህ፥ ሞላዳ፥ ሐጻርሹዓል፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤርሳቤህም፥ በሰምዓም፥ በሞላዳ፥ በሐጸርሱዓል፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤርሳቤህም፥ በሞላዳ፥ በሐጸርሹዓል፥ |
አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፥ እንጀራንም ወሰደ፥ የውኃ አቁማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፥ ብላቴናውንም ሰጥቶ አስወጣት፥ እርሷም ሄደች በቤርሳቤህም ምድረ በዳ ተቅበዘበዘች።
ለሰሜኢም ዐሥራ ስድስት ወንዶችና ስድስት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ለወንድሞቹ ግን ብዙ ልጆች አልነበሩአቸውም፥ ወገናቸውም ሁሉ እንደ ይሁዳ ልጆች አልተባዙም።
በደቡብም በኩል በምድራቸው ዳርቻ አጠገብ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ያሉት የይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ቀብሴኤል፥ ዔደር፥ ያጉር፥
የይሁዳ ልጆች ግዛት በሆነው ክፍል ውስጥ የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ፥ የይሁዳም ልጆች ድርሻ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸው መካከል ወረሱ።