1 ዜና መዋዕል 29:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕንቁም ያለው ሰው ሁሉ ለእግዚአብሔር ቤት ለሆነው ቤተ መዛግብት በጌድሶናዊው በይሒኤል እጅ ሰጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የከበሩ ድንጋዮች ያለውም ሁሉ፣ በጌርሶናዊው በይሒኤል አማካይነት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት አስገባ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከበረ ድንጋይ የነበራቸው ሁሉ የሌዋዊው የጌርሾን ጐሣ አባል የሆነው ይሒኤል ለሚያስተዳድረው ለቤተ መቅደሱ ግምጃ ቤት በስጦታ ስም አቀረቡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከበረ ዕንቍም ያላቸው ሰዎች ሁሉ ለእግዚአብሔር ቤት ለሆነው ቤተ መዛግብት በጌድሶናዊው በኢዩኤል እጅ ሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዕንቍም ያለው ሰው ሁሉ ለእግዚአብሔር ቤት ለሆነው ቤተ መዛግብት በጌድሶናዊው በይሒኤል እጅ ሰጠ። |
ልቡ ያነሣሣውና መንፈሱ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ ሰው ሁሉ ለመገናኛው ድንኳን ሥራና ለአገልግሎቱ ሁሉ ለተቀደሰውም ልብስ የሚሆን ለጌታ ስጦታ አመጡ።