በተለይም በዕድሜ እየሸመገለ በሄደ መጠን ለባዕዳን አማልክት እንዲሰግድ አደረጉት፤ ሰሎሞን እግዚአብሔርን በታማኝነት በማገልገል እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሆኖ አልተገኘም።
1 ዜና መዋዕል 28:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትእዛዜንና ፍርዴንም በማድረግ እንደ ዛሬው ቢጸና መንግሥቱን ለዘለዓለም አጸናዋለሁ።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁን እንደሚያደርገው ሁሉ፣ ትእዛዞቼንና ሕጎቼን ምን ጊዜም ሳያወላውል የሚፈጽም ከሆነ፣ መንግሥቱን ለዘላለም አጸናታለሁ።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘እርሱ አሁን በሚያደርገው ዐይነት ዘወትር ሕጎቼንና ትእዛዞቼን በጥንቃቄ የሚፈጽም ከሆነ፥ መንግሥቱን ለዘለዓለም አጸናለታለሁ’ ብሎአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትእዛዜንና ፍርዴንም መጠበቅ ቢችልና እንደ ዛሬው ቢጸና መንግሥቱን ለዘለዓለም አጸናዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትእዛዜንና ፍርዴንም በማድረግ እንደ ዛሬው ቢጸና መንግሥቱን ለዘላለም አጸናዋለሁ፤’ አለኝ። |
በተለይም በዕድሜ እየሸመገለ በሄደ መጠን ለባዕዳን አማልክት እንዲሰግድ አደረጉት፤ ሰሎሞን እግዚአብሔርን በታማኝነት በማገልገል እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሆኖ አልተገኘም።
ጌታ ስለ እስራኤል ሙሴን ያዘዘውን ሥርዓትና ፍርድ ለመፈጸም ብትጠነቀቅ በዚያን ጊዜ ይከናወንልሃል፤ አይዞህ፥ በርታ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥ።
አሁንም የጌታ ጉባኤ እስራኤል ሁሉ እያዩ፥ አምላካችንም እየሰማ፥ ይህችን መልካሚቱን ምድር እንድትወርሱ፥ ለልጆቻችሁም ለዘለዓለም እንድታወርስዋት የአምላካችሁን የጌታን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ፥ ፈልጉም።