Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 22:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ጌታ ስለ እስራኤል ሙሴን ያዘዘውን ሥርዓትና ፍርድ ለመፈጸም ብትጠነቀቅ በዚያን ጊዜ ይከናወንልሃል፤ አይዞህ፥ በርታ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ለእስራኤል የሰጠውን ሕጉንና ሥርዐቱን ተጠንቅቀህ ብትጠብቅ ይሳካልሃል፤ አይዞህ ጠንክር፤ በርታ፤ ተስፋም አትቍረጥ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ለእስራኤል የሰጠውን ሕጎችንና ሥርዓቶችን ሁሉ ብትፈጽም፥ ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ በርታ፤ ቈራጥ ሁን፤ አትፍራ፤ ተስፋም አትቊረጥ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እስ​ራ​ኤል ሙሴን ያዘ​ዘ​ውን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ ብት​ጠ​ነ​ቀቅ በዚ​ያን ጊዜ ይከ​ና​ወ​ን​ል​ሃል፤ አይ​ዞህ፥ በርታ፤ አት​ፍራ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጥም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እግዚአብሔር ስለ እስራኤል ሙሴን ያዘዘውን ሥርዐትና ፍርድ ታደርግ ዘንድ ብትጠነቀቅ በዚያን ጊዜ ይከናወንልሃል፤ አይዞህ፤ በርታ፤ አትፍራ፤ አትደንግጥ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 22:13
25 Referencias Cruzadas  

“እነሆ እኔ ሰው ሁሉ እንደሚሞት የምሞትበት ጊዜ ተቃርቧል፤ እንግዲህ በርታ! ቆራጥ ሰው ሁን፤


አምላክህ ጌታ እንድታደርግ የሚያዝህን ሁሉ አድርግ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ የምታደርገው ማንኛውም ነገር እንዲከናወንልህ በሙሴ አማካይነት በተሰጠው ሕግ የተጻፉትን የእግዚአብሔርን ሕግና ትእዛዝ፥ ሥርዓትና ፈቃድ ሁሉ ጠብቅ፤


አሁንም፥ እነሆ፥ ጌታ ለመቅደስ የሚሆን ቤትን እንድትሠራ መርጦሃልና በርትተህ በቈራጥነት ፈጽመው።”


ዳዊትም ልጁን ሰሎሞንን እንዲህ አለው፦ “ጠንክር፥ አይዞህ፥ አድርገውም፤ አምላኬ እግዚአብሔር አምላክ ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ፥ አትደንግጥም፥ ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የሚሆነው ሥራ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ እርሱ አይተውህም፥ አይጥልህምም።


ትእዛዜንና ፍርዴንም በማድረግ እንደ ዛሬው ቢጸና መንግሥቱን ለዘለዓለም አጸናዋለሁ።’


ምድሪቱ ሰላም ሰፍኖባት ስለ ነበር በይሁዳ የተመሸጉትን ከተሞችን ሠራ፤ እንዲሁም ጌታ ዕረፍትን ሰጠጥቶት ስለ ነበር በዚያም ዘመን ጦርነት አልነበረበትም።


ማልደውም በመነሣት ወደ ቴቁሔ ምድረ በዳ ወጡ፤ ሲወጡም ኢዮሣፍጥ ቆመና እንዲህ አለ፦ “ይሁዳና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ! ስሙኝ፤ በአምላካችሁ በጌታ እመኑ፥ ትጸኑማላችሁ፤ በነቢያቱም እመኑ፥ ነገሩም ይሳካላችኋል።”


ጌታንም መፍራት ባስተማረው ዘካርያስ በእርሱም ዘመን ጌታን ለመፈለግ ልቡን አቀና፤ ጌታንም በፈለገ ጊዜ ጌታ ነገሩን አከናወነለት።


“ጽኑ፥ አይዞአችሁ፤ ከእኛም ጋር ያለው ከእርሱ ጋር ካለው ይበልጣልና የአሦርን ንጉሥና ከእርሱ ጋር ያለውን ጭፍራ ሁሉ አትፍሩ፥ አትደንግጡም።


እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለ፥ ፍሬውን በየጊዜው እንደሚሰጥ፥ ቅጠሉም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፥ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።


ትእዛዞችህንም ሁሉ ስመለከት በዚያን ጊዜ አላፍርምና።


ስለ ሰሎሞን።


አሁን ግን፥ ዘሩባቤል ሆይ፥ በርታ፥ ይላል ጌታ፤ ታላቁ ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ፥ በርታ፤ እናንተም የአገሩ ሕዝብ ሆይ፥ በርቱ፥ ይላል ጌታ፤ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና ሥሩ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እናንት፥ መቅደሱ እንዲሠራ የሠራዊት ጌታ ቤት ከተመሠረተበት ቀን ጀምሮ ከነቢያት አፍ ይህን ቃል በዚህ ዘመን የሰማችሁ፥ እጃችሁን አበርቱ።


ኢየሱስ ግን “እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና ለአሁን ፍቀድልኝ፤” ሲል መለሰለት፥ ያንጊዜ ፈቀደለት።


እርሱንም ከሻረው በኋላ ዳዊትን በእነርሱ ላይ እንዲነግሥ አስነሣው፤ ሲመሰክርለትም ‘እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ፤’ አለ።


ንቁ፤ በእምነት ጽኑ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ፤


የእርስ በርሳችሁን ሸክም ተሸከሙ፥ በዚህም የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ።


በተረፈ በጌታ በኃይሉ ብርታትም ጠንክሩ።


እንግዲህ ልጄ ሆይ! አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ።


በመጽሐፍ፥ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” ተብሎ የተጻፈውን ንጉሣዊ ሕግ ብትፈጽሙ መልካም ታደርጋላችሁ።


በትእዛዝህ የሚያምፅ ሁሉ የምታዝዘውንም ቃል ሁሉ የማይሰማ፥ እርሱ ይገደል፤ ብቻ ጽና፥ አይዞህ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos