1 ዜና መዋዕል 28:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የካህናቱንና የሌዋውያኑንም ክፍላቸውን በጌታም ቤት ለሚያገልግሉበት ሥራ ሁሉ አስታወቀው። በጌታም ቤት ለሚያገለግሉበት ዕቃ ሁሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም የካህናቱንና የሌዋውያኑን አመዳደብ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ሥራና ለአገልግሎቱ ስለሚጠቀምባቸው ዕቃዎች ሁሉ መመሪያ ሰጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ዳዊት ስለ ካህናትና ሌዋውያን የተለያየ የሥራ ድርሻ፥ በቤተ መቅደሱ ስለሚከናወኑት ተግባሮችና እግዚአብሔርን ለማምለክ አገልግሎት መጠቀሚያ ለሆኑት ዕቃዎች ለሚደረገው እንክብካቤ ዕቅድ ለሰሎሞን ሰጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካህናቱንና የሌዋውያኑንም ክፍላቸውን፥ በእግዚአብሔርም ቤት ለሚያገለግሉበት ሥራ ሁሉ፥ በእግዚአብሔርም ቤት ለሚያገለግሉበት ዕቃ ሁሉ፥ ለአገልግሎት ሁሉ ለሚሆነውም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካህናቱንና የሌዋውያኑንም ክፍላቸውን በእግዚአብሔርም ቤት ለሚያገልግሉበት ሥራ ሁሉ አስታወቀው። በእግዚአብሔርም ቤት ለሚያገለግሉበት ዕቃ ሁሉ፥ |
እነሆም፥ ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ሁሉ የሚሆኑ የካህናትና የሌዋውያን ክፍሎች በዚህ አሉ፤ ለሁሉም ዓይነት አገልግሎትና ሥራ በብልሃትና በነፍሱ ፈቃድ የሚሠራ ሁሉ ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አለቆችና ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው ይታዘዙሃል።”
በአራተኛውም ቀን ብሩ፥ ወርቁና ዕቃዎቹም በአምላካችን ቤት በካህኑ በኡሪያ ልጅ በምሬሞት እጅ ተመዘነ፤ ከእርሱም ጋር የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር ነበረ። ከእነርሱም ጋር ሌዋውያኑ የኢያሱ ልጅ ዮዛባድና የቢኑይ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ።