1 ዜና መዋዕል 26:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለልጁም ለሸማያ ደግሞ ልጆች ተወለዱለት፤ ጽኑዓንም ኃያላን ነበሩና በአባታቸው ቤት ሠለጠኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ልጁ ሸማያ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም በቂ ችሎታ ስለ ነበራቸው የአባታቸው ቤት መሪዎች ሆነው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዖቤድኤዶም የበኲር ልጅ ሸማዕያ ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ዖትኒ፥ ረፋኤል፥ ዖቤድ፥ ኤልዛባድ ኤሊሁና ሰማክያ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እነርሱም ስለ ነበራቸው ታላቅ ችሎታ በጐሣቸው መሪዎች ነበሩ፤ በተለይ የመጨረሻዎቹ ሁለቱ ከፍ ያለ ችሎታ ነበራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለልጁ ለሰማያም ከበኵር ልጁ ከሮሲ ልጆች ተወለዱለት፤ እነርሱም በአባታቸው ቤት የሠለጠኑ እጅግም ኀያላን ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለልጁም ለሸማያ ደግሞ ልጆች ተወለዱለት፤ ጽኑዓንም ኀያላን ነበሩና በአባታቸው ቤት ሠለጠኑ። |
የሸማያ ልጆች፤ ዖትኒ፥ ራፋኤል፥ ዖቤድ፥ ኤልዛባድ ነበሩ፤ ኤልዛባድም ኃያላን ወንድሞች የነበሩት እነርሱም ኤሊሁና ሰማክያ ነበሩ። እነዚህ ሁሉ የዖቤድ-ኤዶም ልጆች ነበሩ፤