ከእነርሱም ጋር በሁለተኛው ደረጃ ያሉትን ወንድሞቻቸውን ዘካርያስን፥ ቤንን፥ ያዝኤልን፥ ሰሚራሞትን፥ ይሒኤልን፥ ዑኒን፥ ኤልያብን፥ በናያስን፥ መዕሤያን፥ መቲትያን፥ ኤሊፍሌሁን፥ ሚቅኔያን፥ ደጁንም የሚጠብቁትን ዖቤድ-ኤዶምንና ይዒኤልን ሾሙ።
1 ዜና መዋዕል 25:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፊተኛው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለነበረው ለዮሴፍ ወጣ፤ ሁለተኛው ለጎልዶያስ ወጣ፤ እርሱ ወንድሞቹም ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመጀመሪያው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለሆነው ለዮሴፍ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12 ሁለተኛው ለጎዶልያስ ወጣ፤ እርሱን ጨምሮ ለቤተ ዘመዶቹና ለወንዶች ልጆቹ፤ ቍጥራቸውም 12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመጀመሪያው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለዮሴፍ ወጣ፤ እርሱም፥ ልጆቹም፥ ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ሁለተኛው ለገዳልያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ሦስተኛ ለዛኩር ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። አራተኛው ለይጽሪ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፥ አምስተኛ ለነታንያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ስድስተኛ ለቡቅያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ሰባተኛ ለአሳርኤላ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ስምንተኛው ለያሻዕያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዘጠነኛው ለማታንያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ዐሥረኛው ለሺምዒ ወጣ፤ እርሱም፥ ልጆቹም፥ ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ሁለተኛው ለሐሻብያ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ዐሥራ ሦስተኛው ለሹባኤል ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ዐሥራ አራተኛ ለማቲትያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ አምስተኛው ለያሪሞት ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ሰባተኛው ለዮሽበቃሽ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ዘጠነኛ ለማሎቲ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያኛ ለኤሊአታ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያ አንደኛ ለሆቲር ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያ ሁለተኛ ለጊደልቲ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያ ሦስተኛ ለማሕዚኦት ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያ አራተኛ ለሮሚምቲዔዜር ወጣ፤ እርሱም ልጆቹም፥ ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመጀመሪያው ዕጣ ለአሳፍ ወገን ለዮሴፍ ለወንድሞቹና ለልጆቹ ለዐሥራ ሁለቱ ደረሳቸው፤ ሁለተኛውም ዕጣ ለጎዶልያስ ለልጆቹና ለወንድሞቹ ለዐሥራ ሁለቱ ደረሳቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፊተኛው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለነበረው ለዮሴፍ ወጣ፤ ሁለተኛው ለጎልዶያስ ወጣ፤ እርሱ ወንድሞቹም ልጆቹን አሥራ ሁለት ነበሩ፤ |
ከእነርሱም ጋር በሁለተኛው ደረጃ ያሉትን ወንድሞቻቸውን ዘካርያስን፥ ቤንን፥ ያዝኤልን፥ ሰሚራሞትን፥ ይሒኤልን፥ ዑኒን፥ ኤልያብን፥ በናያስን፥ መዕሤያን፥ መቲትያን፥ ኤሊፍሌሁን፥ ሚቅኔያን፥ ደጁንም የሚጠብቁትን ዖቤድ-ኤዶምንና ይዒኤልን ሾሙ።
ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች ለማገልገል ለዩ፤ በአገልግሎታቸውም ሥራ ይሠሩ የነበሩት ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።