1 ዜና መዋዕል 23:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልንም ሹማምንት ሁሉ፥ ካህናቱንም፥ ሌዋውያኑንም ሰበሰበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም መላውን የእስራኤልን መሪዎች፣ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ዳዊት የእስራኤልን አለቆች እንዲሁም ካህናትንና ሌዋውያንን በሙሉ በአንድነት ሰበሰበ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልንም አለቆች ሁሉ፥ ካህናቱንም፥ ሌዋውያኑንም ሰበሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልንም አለቆች ሁሉ፥ ካህናቱንም፥ ሌዋውያኑንም ሰበሰበ። |
ሌዋውያንም ዕድሜአቸው ሠላሳ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ተቈጠሩ፤ በእያንዳንዳንዱ ነፍስ ወከፍ ተቈጠሩ፤ ድምራቸውም ሠላሳ ስምንት ሺህ ነበር።
ዳዊትም የእስራኤልን አለቆች ሁሉ፥ የነገዶቹንም አለቆች፥ ንጉሡንም በክፍል የሚያገለግሉትን የሠራዊቱ አለቆች፥ ሻለቆቹንም፥ የመቶ አለቆቹንም፥ በንጉሥና በልጆቹ ሀብትና ግዛት ላይ የተሾሙትን፥ ጃንደረቦችንም፥ ጽኑዓን ኃያላኑንም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።
ኢያሱ እስራኤልን ሁሉ ሽማግሌዎቻቸውንም አለቆቻቸውንም ፈራጆቻቸውንም ሹማምንቶቻቸውንም ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔ ሸምግያለሁ፥ ዕድሜዬም ገፍቷል፤
ኢያሱም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴኬም ሰበሰበ፥ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች አለቆቻቸውንም ፈራጆቻቸውንም ሹማምንቶቻቸውንም ጠራ። እነርሱም በጌታ ፊት ቆሙ።