La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 22:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሲዶናውያውንና የጢሮስ ሰዎች ብዙ የዝግባ እንጨት ወደ ዳዊት ያመጡ ነበርና ቍጥር የሌላቸውን የዝግባ እንጨቶች አዘጋጀ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲሁም ሲዶናውያንና ጢሮሳውያን በብዛት ለዳዊት አምጥተውለት ስለ ነበር፣ ስፍር ቍጥር የሌለው የዝግባ ዕንጨት አሰናዳ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የጢሮስና የሲዶን ሕዝብ ቊጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ የሊባኖስ ዛፍ ግንድ እንዲያመጡለት አደረገ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሲዶ​ና​ው​ያ​ንና የጢ​ሮስ ሰዎ​ችም ብዙ የዝ​ግባ እን​ጨት ለዳ​ዊት ያመጡ ነበ​ርና ቍጥር የሌ​ላ​ቸ​ውን የዝ​ግባ እን​ጨ​ቶች አዘ​ጋጀ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሲዶናውያንና የጢሮስ ሰዎች ብዙ የዝግባ እንጨት ወደ ዳዊት ያመጡ ነበርና ቍጥር የሌላቸውን የዝግባ እንጨቶች አዘጋጀ።

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 22:4
5 Referencias Cruzadas  

በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መልዕክተኞችን፥ የዝግባ ዕንጨት፥ አናጢዎችንና ድንጋይ ጠራቢዎችንም ላከ፥ ለዳዊት ቤተ መንግሥት ሠሩለት።


ሰሎሞንም እንዲህ ሲል ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም ላከ፦ “ከአባቴ ከዳዊት ጋር እንዳደረግህ፥ የሚቀመጥበትንም ቤት ለመሥራት የዝግባ እንጨት እንደ ላክኽለት፥ እንዲሁ ለእኔ አድርግ።


ለጠራቢዎችና ለአናጢዎችም ገንዘብ ሰጡ፤ የፋርስም ንጉሥ ቂሮስ እንደ ፈቀደላቸው የዝግባ ዛፍ ከሊባኖስ ወደ ያፎ ባሕር እንዲያመጡ ለሲዶናውያንና ለጢሮሳውያን መብልና መጠጥ ዘይትም ሰጡ።


ወደፊትም ተዘርግቶ እንዳለው ሸለቆች፥ በወንዝ ዳር እንዳሉ አትክልቶች፥ ጌታ እንደ ተከለው ዓልሙን በውኃም ዳር እንዳሉ ዝግባዎች ተዘርግተዋል።