1 ዜና መዋዕል 22:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አምላካችሁ ጌታ ከእናንተ ጋር አይደለምን? በምድርም የሚቀመጡትን በእጄ አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ምድርም በጌታና በሕዝቡ ፊት ተገዝታለችና በዙሪያችሁ ሁሉ ዕረፍትን ሰጥቶአችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አለ፤ “እግዚአብሔር አምላካችሁ እስካሁን ከእናንተ ጋራ አይደለምን? በየአቅጣጫውስ ዕረፍትን ሰጥቷችሁ የለምን? የምድሪቱን ነዋሪዎች በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኛል፤ ምድሪቱም ለእግዚአብሔርና ለሕዝቡ ተገዝታለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አምላካችሁ እግዚአብሔር እስከ አሁን ከእናንተ ጋር አይደለምን? በሁሉም አቅጣጫ ሰላምን ሰጥቶአችሁ የለምን? በዚህች ምድር ላይ ይኖሩ የነበሩትን ሕዝቦች ሁሉ ድል አድርጌ እንድይዛቸው ፈቅዶልኛል፤ እነርሱም ለእናንተና ለእግዚአብሔር ተገዢዎች ሆነዋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አይደለምን? በምድርም የሚቀመጡትን በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ምድርም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ፊት ተገዝታለችና በዙሪያችሁ ከአሉ ጠላቶቻችሁም ሁሉ ዕረፍትን ሰጥቶአችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አይደለምን? በምድርም የሚቀመጡትን በእጄ አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ምድርም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ፊት ተገዝታለችና በዙሪያችሁ ሁሉ ዕረፍትን ሰጥቶአችኋል። |
እነሆ፥ ልጅ ይወለድልሃል፤ እርሱም ሰላም ያለው ሰው ይሆናል፤ በዙሪያው ካሉ ከጠላቶቹ ሁሉ አሳርፈዋለሁ፤ ስሙ ሰሎሞን ይባላልና፥ በዘመኑም ሰላምና ጸጥታን ለእስራኤል እሰጣለሁ።
በይሁዳም ሁሉና በገሊላ በሰማርያም የነበሩት አብያተ ክርስቲያናት በሰላም ኖሩ፤ ታነጹም፤ በእግዚአብሔርም ፍርሃትና በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት እየሄዱ ይበዙ ነበር።
እንግዲህ አሁን አምላካችሁ ጌታ እንደ ተናገራቸው ወንድሞቻችሁን አሳርፎአቸዋል፤ ስለዚህ አሁን ተመለሱ፥ ወደ ቤታችሁና የጌታ ባርያ ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ሂዱ።
እንዲህም ሆነ፤ ከብዙ ዘመን በኋላ፥ ጌታም እስራኤልን በዙሪያቸው ካሉት ጠላቶቻቸው ሁሉ ባሳረፋቸው ጊዜ፥ ኢያሱም በሸመገለ ዕድሜውም በገፋ ጊዜ፥
ጌታዬ የጌታን ጦርነት ስለሚዋጋ ጌታም ለጌታዬ የታመነ ቤት በእርግጥ ለዘለዓለም የሚያጸናለት በመሆኑ፥ እባክህ የእኔን የአገልጋይህን በደል ይቅር በል፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህ።