ስለዚህም ጌታ ከዚያች ዕለት ጥዋት አንሥቶ እስከ ተወሰነው ቀን ድረስ በእስራኤል ላይ ቸነፈር ላከ፤ በዚህም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሰባ ሺህ ሰው አለቀ።
1 ዜና መዋዕል 21:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም በእስራኤል ላይ ቸነፈርን ሰደደ፤ ከእስራኤልም ሰባ ሺህ ሰዎች አለቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ መቅሠፍት ላከ፤ ከእስራኤልም ሰባ ሺሕ ሰው ዐለቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እግዚአብሔር በእስራኤል ሕዝብ ላይ ቸነፈር አመጣ፤ ከሕዝቡም ሰባ ሺህ የሚሆኑት አለቁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ቸነፈርን ሰደደ፤ ከእስራኤልም ሰባ ሺህ ሰዎች ወደቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ቸነፈርን ሰደደ፤ ከእስራኤልም ሰባ ሺህ ሰዎች ወደቁ። |
ስለዚህም ጌታ ከዚያች ዕለት ጥዋት አንሥቶ እስከ ተወሰነው ቀን ድረስ በእስራኤል ላይ ቸነፈር ላከ፤ በዚህም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሰባ ሺህ ሰው አለቀ።
በዚያው ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አሦራውያን ሰፈር አልፎ አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤ በማግስቱ በማለዳ ሰዎች በሚነቁበት ጊዜ ሁሉም ሞተው ተገኙ።
የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቁጠር ጀመረ፥ ነገር ግን አልፈጸመም፤ ስለዚህም በእስራኤል ላይ ቁጣ ወረደ፥ ቁጥራቸውም በንጉሡ በዳዊት መዝገብ አልተጻፈም።
ጌታም ከቤትሼሜሽ ሰዎች ጥቂቱን መታ፤ ምክንያቱም ወደ ጌታ ታቦት ውስጥ በመመልከታቸው ነበር። ከመካከላቸው ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ ጌታ እጅግ ስለ መታቸውም ሕዝቡ አለቀሱ።