ለቂርያት-ይዓሪምም አባት ለሦባል ልጆች ነበሩት፤ ሀሮኤ የመናሕታውያን እኩሌታ።
የቂርያትይዓይሪም አባት የሦባል ዘሮች፤ የመናሕታውያን ነዋሪዎች እኩሌታ፣ ሀሮኤ፤
የቂርያትይዓሪም አባት ሾባል ሌሎችም ልጆች ነበሩት፦ እነርሱም ሔሮኤትና የመኑሖት ጐሣዎች እኩሌታ ነበሩ።
የቀርያታርምም አባት የሶባል ልጆች አረኤ፥ ሃጼ፥ አማኒት ነበሩ።
ለቂርያትይዓሪምም አባት ለሦባል ልጆች ነበሩት፤ ሀሮኤ የመናሕታውያን እኵሌታ።
የቤተልሔም አባት ሰልሞን፥ የቤት-ጋዴር አባት ሐሬፍ።
የቂርያት-ይዓሪምም ወገኖች፤ ይትራውያን፥ ፉታውያን፥ ሹማታውያን፥ ሚሽራውያን ነበሩ፤ ከእነዚህም ጾርዓውያንና ኤሽታኦላውያን ወጡ።
የሰልሞንም ልጆች ቤተልሔም፥ ነጦፋውያን፥ ዓጣሮት-ቤት-ዮአብ፥ የመናሕታውያን እኩሌታ፥ ጾርዓውያን ነበሩ።
የሦባልም ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤትም አሑማይንና ላሃድን ወለደ። እነዚህ የጾርዓውያን ወገኖች ናቸው።
የእስራኤልም ልጆች ተጉዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው መጡ፤ ከተሞቻቸው ገባዖን፥ ከፊራ፥ ብኤሮት፥ ቂርያት-ይዓሪም ነበሩ።