1 ዜና መዋዕል 2:50 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የካሌብ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ የኤፍራታ የበኩሩ የሆር ልጅ የቂርያት-ይዓሪም አባት ሦባል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ሁሉ የካሌብ ዘሮች ነበሩ። የኤፍራታ የበኵር ልጅ የሑር ወንዶች ልጆች፤ ሦባል የቂርያትይዓይሪም አባት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ የሚከተሉትም የካሌብ ዘሮች ናቸው፦ ሑር የካሌብ ከሚስቱ ከኤፍራታ የተወለደው የመጀመሪያው ልጁ ሲሆን የሑር ልጅ የቂርያትይዓሪም አባት ሾባል ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካሌብም ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ የኤፍራታ የበኵሩ የኦር ልጅ የቀርያታርም አባት ሶባል ነበር፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካሌብ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ የኤፍራታ የበኵሩ የሆር ልጅ የቂርያትይዓሪም አባት ሦባል፥ |
ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ከዚያም ተነስቶ ወደ ዔፍሮን ተራራ ከተሞች ወጣ፤ ቂርያት-ይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ታጠፈ፤
በከተማይቱ በር አደባባይም የነበሩ ሽማግሌዎችና ሌሎችም ሰዎች ሁሉ፦ “እኛ ምስክሮች ነን፥ ጌታ ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ሠሩ እንደ ሁለቱ፥ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፥ አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም በቤተልሔም ይጠራ።
የቂርያትይዓሪም ሰዎችም መጥተው የጌታን ታቦት ይዘው ወጡ፤ ከዚያም በኮረብታው ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት ወሰዱት። የጌታን ታቦት እንዲጠብቅም ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት።