የዮናታንም ልጆች ፌሌትና ዛዛ ነበሩ፤ እነዚህ የይረሕምኤል ልጆች ነበሩ።
የዮናታን ወንዶች ልጆች፤ ፌሌት፣ ዛዛ። እነዚህ የይረሕምኤል ዘሮች ነበሩ።
ዮናታንም ፔሌትና ዛዛ የተባሉ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የይራሕመኤል ዘሮች ናቸው።
የዮናታንም ልጆች ፋሌትና አዛዝ ነበሩ፤ እነዚህም የኢያሬምሔል ልጆች ነበሩ።
የሸማይም ወንድም የያዳ ልጆች ዬቴርና ዮናታን ነበሩ፤ ዬቴርም ያለ ልጆች ሞተ።
ለሶሳንም ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ ለሶሳንም ኢዮሄል የተባለ ግብጻዊ አገልጋይ ነበረው።