1 ዜና መዋዕል 2:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኤስሮምም የበኩር ልጁ የይረሕምኤል ልጆች በኩሩ ራም፥ ቡናህ፥ ኦሬን፥ ኦጼም፥ አኪያ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኤስሮም የበኵር ልጅ የይረሕምኤል ወንዶች ልጆች፤ የበኵር ልጁ ራም፣ ቡናህ፣ ኦሬን፣ ኦጼም፣ አኪያ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሔጽሮን የበኲር ልጅ ይራሕመኤል አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም የመጀመሪያው ራም ቀጥሎም ቡና፥ ኦሬን፥ ኦጼምና አሒያ ተብለው የሚጠሩ ነበሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤስሮምም የበኵር ልጁ የኢያሬምሄል ልጆች በኵሩ ራም፥ በአናን፥ አራን፥ አሶም፥ አኪያ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኤስሮምም የበኵር ልጁ የይረሕምኤል ልጆች በኵሩ ራም፥ ቡናህ፥ ኦሬን፥ ኦጼም፥ አኪያ ነበሩ። |
አኪሽም፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” ሲል በጠየቀው ጊዜ ዳዊት፥ “የዘመትነው በይሁዳ፥ ወይም በይራሕመኤላውያን፥ ወይም በቄናውያን ላይ ነው” እያለ ይመልስለት ነበር።