ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስልሳ ዓመት በሆነው ጊዜ ወዳገባት ወደ ገለዓድ አባት ወደ ማኪር ልጅ ገባ፤ ሠጉብንም ወለደችለት። ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤
1 ዜና መዋዕል 2:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሠጉብም በገለዓድ ምድር ሀያ ሦስት ከተሞች ነበሩትን ጌሹርን ወለደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤ እርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተሞች ያስተዳድር ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰጉብም ያኢር ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ወለደ፤ ያኢር በገለዓድ ግዛት ውስጥ የሚገኙትን ኻያ ሦስት ከተሞች ይገዛ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴጉብም ኢያኤርን ወለደ፤ ለእርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተሞች ነበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤ ለእርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተሞች ነበሩት። |
ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስልሳ ዓመት በሆነው ጊዜ ወዳገባት ወደ ገለዓድ አባት ወደ ማኪር ልጅ ገባ፤ ሠጉብንም ወለደችለት። ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤
ጌሹርና አራምም የኢያዕርን ከተሞች ከቄናትና ከመንደሮችዋ ጋር ስልሳውን ከተሞች ወሰዱባቸው። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ልጆች ነበሩ።
የምናሴ ልጅ ያኢር፥ ባሳንን እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ ድረስ፥ የአርጎብን ግዛት ሁሉ ወሰደ፥ ይችንም የባሳን ምድር እስከ ዛሬ ድረስ በሚጠራበት የያኢር መንደሮች ብሎ ጠራ።