1 ዜና መዋዕል 18:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሐማትም ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የሱባን ንጉሥ የአድርአዛርን ሠራዊት ሁሉ ድል እንዳደረገ ሰማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሐማት ንጉሥ ቶዑ፣ ዳዊት የሱባን ንጉሥ የአድርአዛርን ሰራዊት ሁሉ ድል እንደ መታ ሲሰማ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሐማት ንጉሥ ቶዒ ዳዊት የጾባን ንጉሥ የሀዳድዔዜርን መላ ሠራዊት ድል እንዳደረገ ሰምቶ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤማትም ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን፥ ጭፍራውንም ሁሉ እንደ መታ ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሐማትም ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የሱባን ንጉሥ የአድርአዛርን ጭፍራ ሁሉ እንደ መታ ሰማ። |
ቶዑም ከአድርአዛር ጋር ሁልጊዜ ይዋጋ ነበርና ዳዊት አድርአዛርን ወግቶ ድል ስለ አደረገው ደኅንነቱን እንዲጠይቀውና እንዲመርቀው ልጁን አዶራምን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የወርቅና የብር የናስም ዕቃ ይዞ መጣ።
የአሞንም ልጆች በዳዊት ዘንድ እንደ ተጠሉ ባዩ ጊዜ ሐኖንና የአሞን ልጆች ከመስጴጦምያ፥ ከአራም-መዓካ፥ ከሱባ ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን ለመቅጠር አንድ ሺህ መክሊት ብር ላኩ።