1 ዜና መዋዕል 18:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም የአድርአዛር ባርያዎች ይሸከሟቸው የነበሩትን የወርቅ ጋሻዎች ወሰደ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም ይዞአቸው መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም የአድርአዛር ጦር አለቆች ያነገቧቸውን የወርቅ ጋሻዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት የሀዳድዔዜር ባለሟሎች የሆኑ ባለሥልጣኖች አንግበውት የነበረውን ከወርቅ የተሠራ ጋሻ ሁሉ ማርኮ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ለአድርአዛር አገልጋዮች የነበሩትን የወርቅ ማርዳዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ይዞአቸው መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ለአድርአዛር ባሪያዎች የነበሩትን የወርቅ ጋሻዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ይዞአቸው መጣ። |
ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ የጦር ሠራዊት አሰፈረ፤ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ ግብርም አመጡለት። ጌታም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድል አድራጊ አደረገው።