La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 18:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ የጦር ሠራዊት አሰፈረ፤ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ ግብርም አመጡለት። ጌታም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድል አድራጊ አደረገው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም በሶርያ ግዛት ውስጥ ባለችው በደማስቆ የጦር ሰፈር አቋቋመ፤ ሶርያውያንም ገባሮቹ ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት። እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚያም በኋላ በግዛታቸው ላይ የጦር ሰፈር አቋቋመ፤ ሕዝቡም ግብር እየከፈለ ለእርሱ ተገዛ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን በየስፍራው ድል አድራጊ አደረገው፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም በደ​ማ​ስቆ ሶርያ ጭፍ​ሮ​ችን አኖረ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ያድ​ነው ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ ጭፍሮች አኖረ፤ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት። እግዚአብሔርም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድል ይሰጠው ነበር።

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 18:6
8 Referencias Cruzadas  

በሄድህበትም ሁሉ ከአንተ ጋር ነበርሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁ፤ በምድርም ላይ እንዳሉ እንደ ታላላቆች ስም የአንተን ስም ታላቅ አደርጋለሁ።


ሞዓብን መታ፤ ሞዓባውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ ግብርም አመጡለት።


ከደማስቆም ሶርያውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ሊረዱ በመጡ ጊዜ ዳዊት ከሶርያውያን ሀያ ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደለ።


ዳዊትም የአድርአዛር ባርያዎች ይሸከሟቸው የነበሩትን የወርቅ ጋሻዎች ወሰደ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም ይዞአቸው መጣ።


ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ጌታ መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል።


ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፥ ድል ግን ከጌታ ዘንድ ነው።


ጌታም ከእርሱ ጋር ስለ ነበር የሚያደርገው ነገር ሁሉ ይሳካለት ነበር።