1 ዜና መዋዕል 17:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ጽኑ ፍቅሬን ከአንተ በፊት ከነበረው ላይ እንደወሰድሁ ከእርሱ ላይ ከቶውንም አልወስድም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል፤ ጽኑ ፍቅሬን ከአንተ በፊት ከነበረው ላይ እንዳራቅሁ ሁሉ፣ ከርሱ ላይ ከቶ አልወስድም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ አንተ በሳኦል እግር ተተክተህ ትነግሥ ዘንድ ከዙፋኑ ባወረድኩት በሳኦል ላይ ባደረግሁት ዐይነት ምሕረቴን ከልጅህ በማራቅ አልተወውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆነኛል፤ ከአንተ አስቀድሞ ከነበሩት እንዳራቅሁ፥ ምሕረቴን ከእርሱ አላርቅም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ከአንተ አስቀድሞ ከነበረው እንዳራቅሁ፥ ምሕረቴን ከእርሱ አላርቅም። |
ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ሰውነታችሁ በሕይወት እንድትኖር ስሙኝ፥ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።