Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 17:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ አንተ በሳኦል እግር ተተክተህ ትነግሥ ዘንድ ከዙፋኑ ባወረድኩት በሳኦል ላይ ባደረግሁት ዐይነት ምሕረቴን ከልጅህ በማራቅ አልተወውም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል፤ ጽኑ ፍቅሬን ከአንተ በፊት ከነበረው ላይ እንዳራቅሁ ሁሉ፣ ከርሱ ላይ ከቶ አልወስድም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እኔም አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ጽኑ ፍቅሬን ከአንተ በፊት ከነበረው ላይ እንደወሰድሁ ከእርሱ ላይ ከቶውንም አልወስድም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ልጄ ይሆ​ነ​ኛል፤ ከአ​ንተ አስ​ቀ​ድሞ ከነ​በ​ሩት እን​ዳ​ራ​ቅሁ፥ ምሕ​ረ​ቴን ከእ​ርሱ አላ​ር​ቅም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ከአንተ አስቀድሞ ከነበረው እንዳራቅሁ፥ ምሕረቴን ከእርሱ አላርቅም።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 17:13
16 Referencias Cruzadas  

ይሁን እንጂ ስሜ እንዲጠራባት በመረጥኳት በኢየሩሳሌም አገልጋዬ ዳዊት በፊቴ አንድ ዘር ይኖረው ዘንድ ለልጁ አንድ ነገድ እሰጠዋለሁ


ቤተ መቅደስ የሚሠራልኝም እርሱ ይሆናል፤ ዙፋኑንም ለዘለዓለም የጸና እንዲሆን አደርጋለሁ፤


በሕዝቤና በመንግሥቴ ላይ ለዘለዓለም እሾመዋለሁ፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ አይኖረውም።’ ”


ቊጣው በቅጽበት ስለሚነድ በእናንተ ላይ ተቈጥቶ እንዳያጠፋችሁ በመንቀጥቀጥ ስገዱለት እርሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ የተባረኩ ናቸው።


“የእግዚአብሔርን ዐዋጅ ዐውጃለሁ፤ እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድኩህ፤


“ጆሮአችሁን አዘንብላችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ቃሌን አድምጡ፤ ዳዊትን እንደ ወደድኩት እናንተን በታማኝነት ለመውደድ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ።


እርሱ ታላቅ ይሆናል፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል፤ ጌታ አምላክ የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል።


ከደመናውም ውስጥ፥ “የመረጥኩት ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት!” የሚል ድምፅ መጣ።


አብ ልጁን ይወዳል፤ ሁሉንም ነገር በእጁ አስረክቦታል።


እኔ አባታችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ ትሆናላችሁ፥ ይላል ሁሉን ቻይ አምላክ።”


እግዚአብሔር ከቶ ከመላእክት መካከል፥ “አንተ ልጄ ነህ፤ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤” ወይም “እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል” ያለው ማንን ነው?


ሳሙኤልም ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “ዛሬ እግዚአብሔር የእስራኤልን መንግሥት ቀዶ ከእጅህ በመውሰድ ለተሻለ ለሌላ ሰው ሰጥቶታል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos