ለውጊያም የተዘጋጁ የዳን ሰዎች ሀያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።
ከዳን ሰዎች ለጦርነት የተዘጋጁ ሃያ ስምንት ሺሕ ስድስት መቶ፤
ለሰልፍም የተዘጋጁ የዳን ሰዎች ሃያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።
ለሰልፍም የተዘጋጁ የዳን ሰዎች ሃያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።
የዳን ልጅ ሑሺም ነው።
ዳን በጐዳና ላይ እንደ እባብ ይሆናል፥ በመንገድም እንደ ቀንዳም እባብ፥ ፈረሱን ከሰኮናው ይነክሳል፥ ፈረሰኛም ወደ ኋላው ይወድቃል።
የንፍታሌምም አለቆች አንድ ሺህ ነበሩ፥ ከእነርሱም ጋር ጋሻና ጦር የታጠቁ ሠላሳ ሰባት ሺህ ነበሩ።
በጽኑ የሠለጠኑ ተዋጊዎች፥ ለውጊያም የተዘጋጁ የአሴር ሰዎች አርባ ሺህ ነበሩ።
በቅበቃር፥ ኤሬስ፥ ጋላል፥ የአሳፍ ልጅ የዝክሪ ልጅ የሚካ ልጅ መታንያ ነበር፤
ስለ ዳንም እንዲህ አለ፥ “ዳን የአንበሳ ደቦል ነው፥ ከባሳን ዘልሎ ይወጣል።”