ዘኍል 3:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማደሪያውንም ሥራ ይሠሩ ዘንድ፥ እርሱንና ማኅበሩን ሁሉ ለማገልገል የሚያስፈልገውን ነገር በመገናኛው ድንኳን ፊት ይጠብቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመገናኛው ድንኳን የማደሪያውን አገልግሎት በመፈጸም ለርሱና ለማኅበረ ሰቡ ሁሉ የሚያስፈልጉትን ተግባሮች ያከናውኑ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማደሪያውንም ሥራ እየሠሩ፥ በመገናኛው ድንኳን ፊት ለእርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ያለባቸውን ግዴታዎች ይፈጽሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም አሮንንና መላውን ማኅበር በመገናኛው ድንኳን በማገልገል ተግባራቸውን ይፈጽማሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የድንኳኑን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ሕጉንና የእስራኤልን ልጆች ሕግ በምስክሩ ድንኳን ፊት ይጠብቁ። |
ይህ ሰሎሚትና ወንድሞቹ ንጉሡ ዳዊትና የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች የሠራዊቱም አለቆች፥ በቀደሱት በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ሁሉ ላይ ተሾመው ነበር።
ነገር ግን በምስክሩ ማደሪያና በዕቃዎች ሁሉ ለእርሱም በሚሆነው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋውያንን አቁማቸው። ማደሪያውንና ዕቃዎችን ሁሉ ይሸከሙ፥ ያገልግሉትም፥ በማደሪያውም ዙሪያ ይስፈሩ።
ከእስራኤልም ልጆች ድርሻ ከሰዎች ከበሬዎችም ከአህዮችም ከመንጎችም ከከብቶችም ሁሉ ከአምሳ አንድ ትወስዳለህ፥ የእግዚአብሔርንም ማደሪያ አገልግሎት ለሚጠብቁ ለሌዋውያን ትሰጣለህ።