ዘኍል 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተቀቡ ካህናት በክህነትም ያገለግሉ ዘንድ የቀደሳቸው የአሮን ልጆች ስም ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ለክህነት አገልግሎት የለያቸው፣ ካህናት ለመሆን የተቀቡት የአሮን ወንድ ልጆች ስም ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሮን ልጆች፥ እርሱም በክህነት አገልግሎት እንዲያገለግሉ የቀደሳቸው፥ የተቀቡ ካህናት ስሞቻቸው እነዚህ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህም በክህነት እንዲያገለግሉ ተቀብተው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በክህነት ያገለግሉ ዘንድ የተቀቡና እጆቻቸውን የተቀደሱ የአሮን ልጆች ስም ይህ ነው። |
ይህንም ሁሉ ወንድምህን አሮንን ከእርሱም ጋር ልጆቹን ታለብሳቸዋለህ፤ በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀባቸዋለህ፥ ትክናቸዋለህ፥ ትቀድሳቸውማለህ።
ሙሴም ከቅብዓቱ ዘይትና በመሠዊያው ላይ ካለው ከደሙ ወስዶ በአሮንና በልብሱ ላይ፥ በልጆቹና በልጆቹ ልብስ ላይ ረጨው፤ አሮንንና ልብሱንም፥ ልጆቹንም፥ የልጆቹንም ልብስ ቀደሰ።
ናዳብና አብዩድ በሲና ምድረ በዳ በእግዚአብሔር ፊት ልዩ እሳት ባቀረቡ ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ሞቱ፤ ልጆችም አልነበሩአቸውም። አልዓዛርና ኢታምር በአባታቸው በአሮን ፊት በክህነት ያገለግሉ ነበር።