ኢያሱ 15:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ወጣ፥ ወደ ጺንም አለፈ፥ በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ወጣ፥ በሐጽሮንም በኩል አለፈ፥ ወደ አዳርም ወጣ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የአቅረቢምን መተላለፊያ በማቋረጥ በጺን በኩል እስከ ቃዴስ በርኔ ደቡባዊ ክፍል ይደርሳል፤ ደግሞም ሐጽሮንን ዐልፎ ወደ አዳር ይወጣና ወደ ቀርቃ ይታጠፋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ወጣ፥ ወደ ጺንም አለፈ፥ በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ወጣ፥ በሐጽሮንም በኩል አለፈ፥ ወደ አዳርም ወጣ፥ ወደ ቀርቃ ዞረ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ደቡብ አቅጣጫ ከዐቅራቢም መተላለፊያ እስከ ጺን ይደርሳል፤ በቃዴስ በርኔ ደቡብም በኩል ሔጽሮንን አልፎ ወደ አዳር ከፍ ይልና ወደ ቃርቃ አቅጣጫ ይታጠፋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም በአቅረቢን ዐቀበት ፊት ይሄዳል፤ ወደ ጺንም ይወጣል፤ በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ይወጣል፤ በአስሮንም በኩል ያልፋል፤ ወደ ሰራዳም ይወጣል፥ ወደ ቃዴስ ምዕራብም ይዞራል። |
የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በመጀመሪያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጡ፤ ማርያምም በዚያ ሞተች፥ በዚያም ተቀበረች።
ዳርቻችሁም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ይዞራል ወደ ጺንም ያልፋል፤ መውጫውም በቃዴስ በርኔ በደቡብ በኩል ይሆናል፤ ወደ ሐጸርአዳር ይሄዳል ወደ ዓጽሞንም ያልፋል፤
ወደ ቀርቃ ዞረ፥ ወደ አጽሞንም አለፈ፥ በግብፅም ወንዝ በኩል ወጣ፥ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ፥ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው።