ቤንሀዳድም ለንጉሡ ለአሳ እሺ አለው፤ የሠራዊቱንም አለቆች በእስራኤል ከተሞች ላይ ሰድዶ ዒዮንንና ዳንን፥ አቤልቤት መዓካንና ኪኔሬትን ሁሉ የንፍታሌምንም አገር ሁሉ መታ።
ኢያሱ 11:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰሜንም በተራራማው አገር፥ በኪኔሬትም ደቡብ በዓረባ፥ በቈላውም፥ በምዕራብም በኩል ባለ በዶር ኮረብታ ወደ ነበሩ ነገሥታት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም በተራራማው አገር ከኪኔሬት ደቡብ በዓረባ፣ በምዕራቡ ቈላ አገርና ከዶር ኰረብታ በስተምዕራብ ወዳሉት ነገሥታት ላከ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰሜንም በተራራማው አገር፥ በኪኔሬትም ደቡብ በዓረባ፥ በቈላውም፥ በምዕራብም በኩል ባለ በዶር ኮረብታ ወደ ነበሩ ነገሥታት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰሜን በኩል በኮረብታማው አገር፥ ከገሊላ ባሕር በስተ ደቡብ ወደ ነበሩበት ነገሥታት፥ በዮርዳኖስ ሸለቆ፥ በኮረብታዎቹ ግርጌ በስተምዕራብም በፎት ዳር ወደ ነበሩት ነገሥታት ላከ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመስዕም በተራራማው ሀገር ፥ በከነሬትም ዐዜብ በዓረባ፥ በቆላውም ባለ በፊናዶር ሸለቆ ወደ ነበሩ ነገሥታት፥ |
ቤንሀዳድም ለንጉሡ ለአሳ እሺ አለው፤ የሠራዊቱንም አለቆች በእስራኤል ከተሞች ላይ ሰድዶ ዒዮንንና ዳንን፥ አቤልቤት መዓካንና ኪኔሬትን ሁሉ የንፍታሌምንም አገር ሁሉ መታ።
እንዲሁም ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ተራራማውን አገር ደቡቡንም ቈላውንም ቁልቁለቱንም ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ መታ፥ ማንንም አላስቀረም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም ነፍስ ያለበትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።
የገባዖንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ልከው፦ ባሪያዎችህን ለመርዳት እጅህን አትመልስ፥ በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ፈጥነህ ወደ እኛ ውጣ አድነንም እርዳንም አሉት።
ኢያሱም ያን ምድር ሁሉ፥ ተራራማውን፥ ደቡቡንም ሁሉ፥ የጎሶምንም ምድር ሁሉ፥ ቈላውንም፥ ዓረባንም፥ የእስራኤልንም ተራራማውንና ቈላውን ያዘ፥
በዚያን ጊዜም ኢያሱ መጣ፥ ከተራራማውም አገር ከኬብሮንም ከዳቤርም ከአናብም ከእስራኤልም ተራራማ ሁሉ ከይሁዳም ተራራማ ሁሉ የዔናቅን ልጆች ገደለ፥ ኢያሱም ከከተሞቻቸው ጋር ፈጽሞ አጠፋቸው።
በምሥራቅም በኩል ያለውን ዓረባ እስከ ኪኔሬት ባሕር ድረስ፥ በቤትየሺሞት መንገድ አጠገብ እስካለው እስከ አረባ ባሕር እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ በደቡብም በኩል ከፈስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለውን ምድር የገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን፥
በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ቅሬታ ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኪኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበር።
በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤትሳንና መንደሮችዋ ይብልዓምና መንደሮችዋ፥ ዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ዓይነዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ታዕናክና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ መጊዶና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ሦስቱ ኮረብቶች ለምናሴ ነበሩ።
ምናሴም የቤትሳንንና የመንደሮችዋን፥ የታዕናክንና የመንደሮችዋን፥ የዶርንና የመንደሮችዋን፥ የይብለዓምንና የመንደሮችዋን፥ የመጊዶንና የመንደሮችዋን ሰዎች አላወጣቸውም፥ ነገር ግን ከነዓናውያን በዚያ አገር በመቀመጥ ጸኑ።