ሁለት የወይራ ዛፎች፥ አንዱ በማሰሮው በስተ ቀኝ አንዱም በስተ ግራው ሆነው፥ በአጠገቡ ነበሩ አልሁ።
ደግሞም አንዱ ከዘይቱ ማሰሮ በስተቀኝ፣ ሌላውም በስተግራ የሆኑ ሁለት የወይራ ዛፎች አሉ።”
በተጨማሪም ሁለት የወይራ ዛፎች፥ አንዱ በማሰሮው በስተ ቀኝ አንዱም በስተ ግራው ነበሩ” አልኩት።
በመቅረዙም አጠገብ ሁለት የወይራ ዛፎች በማሰሮው ግራና ቀኝ ይታያሉ፤”
የብር ድሪ ሳይበጠስ፥ የወርቅም ኵስኵስት ሳይሰበር፥ ማድጋውም በምንጭ አጠገብ ሳይከሰከስ፥ ወደ መስኮት የሚያዩ ዐይኖች ሳይጠፉ፥ የአደባባይ ደጆች ሳይዘጉ፥ ስለ ቃላት ድንጋጤ ከጠላት ቃል የተነሣ የሚጮኹ ሳይነሡ፥ በአዳም ልጆች ሁሉ ወዮታ ሳይሆን፥ ወደ ላይም ሳይመለከቱ፥ በመንገድም ፍርሀት ሳይመጣ፥ እሳትም ወደ ላይ ከፍ ማለትን በወደደ ጊዜ ሳይታይ፥ በአደባባይ ልቅሶ ሳይሰማ፥ የብር መልኩ ሳይለወጥ፥ የወርቅም መልኩ ሳይጠፋ፥ መንኰራኵሩም በጕድጓድ ላይ ሳይሰበር፥
እርሱም፦ በምድር ሁሉ ጌታ አጠገብ የቆሙት ሁለቱ የተቀቡት እነዚህ ናቸው አለኝ።
ከቅርንጫፎችዋ አንዳንዶቹ ቢሰበሩ የዱር ወይራ የሆንህ አንተን በእነርሱ ፋንታ ተከሉ፤ የእነርሱንም ሥርነት አገኘህ፤ እንደ እነርሱም ዘይት ሆንኽ።
አንተ የዱር ወይራ፥ አንተን ስንኳ ከበቀልህበት ቈርጦ ባልበቀልህበት በመልካሙ ዘይት ስፍራ ከተከለህ፥ ይልቁን ጥንቱን ዘይት የነበሩትን እነዚያን በበቀሉበት ስፍራ እንዴት አብልጦ ሊተክላቸው አይችልም?
እነዚህ በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ ሁለቱ ወይራዎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው።
ወይራዋ ግን፦ እግዚአብሔር ሰዎችን የሚያከብርበትን ቅባቴን ትቼ በዛፎች ላይ ለመንገሥ ልሂድን? አለቻቸው።