ለክፋት የሚደክም ሰው ግን ከዚያ ጭቃ ከንቱ ጣዖትን ይሠራል፥ ይህም ከጥቂት ቀን አስቀድሞ ከምድር ተሠራ፤ ከጥቂት ቀንም በኋላ ከእርሷ ወደ ወጣባት ምድር ይመለስ ዘንድ አለው፥ ስለ ነፍሱ ፍርድም ይመረመራል።
ከንቱ ድካም እርሱ ራሱ በቅርቡ ከወጣበት አፈር፥ ብዙም ሳይቆይ የተዋሳትን ነፍስ እንዲመልስ በተጠየቀ ጊዜ ከሚገባበት ምድር፥ ከዚያው ጭቃ ፍሬ ቢሱን ጣኦት ቀረጸ።