እርሱ መዋቲ ሲሆን በኀጢአት እጅ መዋቲን ይሠራል፥ እርሱ ሕያው ስለሆነ እነዚህ ግን ከቶ ሕያዋን ስላይደሉ ከጣዖቶቹ ይሻላልና።
ሞት ዕጣ ፈንታው ነውና ያልተባረኩት እጆቹ ሊሠሩ የሚችሉት በድን ብቻ ነው። ከሚያመልካቸው ጣኦቶች ይልቅ፥ እርሱ የከበረ ነው፤ እርሱ መኖር ይችላል፥ እነርሱ ግን ፈጽሞ ሊኖሩ አይችሉም።