ስለ መንገድም ነገር ይንቀሳቀስ ዘንድ ወደማይቻለውና አንዲት ርምጃን ወደማይራመደው ይለምናል። ስለ ብልጽግናና ስለ ሥራም፥ ስለ ማግኘትም፥ የእጅን ሥራም ስለ ማቅናት እጆቹ ምንም ወደማይሠሩ ይለምናል፥ ኀይልንና ሥራ ማፍጠንንም ይሰጠው ዘንድ ምንም ኀይል ከሌለው ከእርሱ ይፈልጋል።
ስለ ትርፍ፥ ስለ ወደ ፊት ተግባሩና ስለሙያ ትጋቱ ጥበብን ይሰጠው ዘንድ፥ እጆቹ ከቶውንም ሰርተው ከማያውቁት ይለምናል።