በነቢያቱ ቃልና በቅዱሳት መጻሕፍት አስቀድሞ በተስፋ ያናገረው፥
ስለዚህ ወንጌል በነቢያቱ በኩል በቅዱሳት መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ተሰጠ።
ይህም ወንጌል እግዚአብሔር አስቀድሞ በነቢያቱ አማካኝነት በቅዱሳን መጻሕፍት የሰጠው ተስፋ ነው፤
ይህም ወንጌል እግዚአብሔር በነቢያት አማካይነት በቅዱሳት መጻሕፍት አስቀድሞ የሰጠው የተስፋ ቃል ነው።
በነቢይ ከጌታ ዘንድ፥
ከጥንት ጀምሮ በነበሩ በቅዱሳን በነቢያት አፍ እንደ ተናገረ።
ለሚያምኑበትም ሁሉ ኀጢአታቸው በስሙ እንደሚሰረይላቸው ነቢያት ሁሉ ምስክሮቹ ናቸው።”
“እኛም እግዚአብሔር ለአባቶቻችን ያናገረላቸውን ተስፋ እንነግራችኋለን።
አሁንም ከጥንት ጀምሮ በእግዚአብሔር ዘንድ ለአባቶቻችን የተሰጠውን ተስፋ በመታመን ከፍርድ በታች ቆሜአለሁ።
ብቻውን ጠቢብ ለሆነው ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን፤ አሜን።
በሁሉ ነገር ብዙ ነው፤ ነገር ግን ከዚያ አስቀድሞ የእግዚአብሔር ቃል አደራ ተሰጣቸው።
አሁን ግን በኦሪትና በነቢያት የተመሰከረላት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ኦሪት ተገለጠች።