መዝሙር 87:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ፥ በታችኛው ጕድጓድ አስቀመጡኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሕዝቡን ሲመዘግብ፣ “ይህ ሰው የተወለደው በዚያ ነው” ብሎ ይጽፋል። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እያለ ሕዝቦችን ይመዘግባል። “እገሌ በውስጥዋ ተወለደ” እያለ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሕዝቦችን ሁሉ ይመዘግባል፤ እያንዳንዱንም “በጽዮን የተወለደ” ብሎ ይጠራዋል። |
“እኔም፦ ይሁን አልሁ፤ በወንዶች ልጆች መካከል እሾምሃለሁ፤ አሕዛብን የሚገዛ ሁሉን ቻይ የሆነ የእግዚአብሔርን ርስት የተመረጠችውን ምድር ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ አባቴ ትለኛለህ፤ ከእኔም አትመለስም አልሁ ብለሃልና።
እጄም ሐሰተኛ ራእይን በሚያዩ፥ ሕዝቤንም ለማታለል በከንቱ በሚያምዋርቱ ነቢያት ላይ ትሆናለች። እነርሱም በሕዝቤ ማኅበር ውስጥ አይኖሩም፤ በእስራኤልም ቤት መጽሐፍ አይጻፉም፥ ወደ እስራኤልም ምድር አይገቡም፤ እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
እግዚአብሔርም፥ “በከተማዪቱ በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ኀጢአት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግንባር ላይ ምልክት ጻፍ አለው።
ወንድሜና አጋዤ ስትሪካ ሆይ፥ እንድትረዳቸው አንተንም እለምንሃለሁ፤ ወንጌልን በማስተማር ከቀሌምንጦስና ሥራቸው ከተባበረ፥ ስማቸውም በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፈላቸው ከወንድሞቻችንም ሁሉ ጋር ከእኔም ጋር ደክመዋልና።