አንተ ባሕርን በኀይልህ አጸናሃት፤ አንተ የእባቡን ራስ በውኃ ውስጥ ሰበርህ።
ለካ ልቤን ንጹሕ ያደረግሁት በከንቱ ነው፤ እጄንም በየዋህነት የታጠብሁት በከንቱ ኖሯል!
እንዲህም አልሁ፦ በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁ፥ እጆቼንም በንጽሕና በከንቱ አጠብሁ።
ሐሳቤን በቅንነት መጠበቄና በደልንም ከመሥራት መቈጠቤ ምን ጠቀመኝ?
እንገዛለትስ ዘንድ እርሱ ምን ይችላል? ወይስ ወደ እርሱ ብንቀርብ ምን ይጠቅመናል?
ሰው ከእግዚአብሔር ጕብኝት ሲኖረው እግዚአብሔር አይጐበኘውም አትበል።
ኀጢአት ብሠራስ ምን አደርጋለሁ? ትላለህ።
እኔ ብናገር የሚጠቅመኝ የለም፤ ፊቴም በጩኸት ወደቀ፤
“ኃጢኣተኛ ሰው ከሆንሁ፤ ስለ ምን አልሞትሁም?
በአዘቅት ውስጥ ታሰጥመኛለህ፤ ልብሴም ይጸየፈኛል።
አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፤ ፍለጋህንም አስተምረኝ።
እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፤ ዞርሁ በድንኳኑም መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ እልልም አልሁለት እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፥ እዘምርለትማለሁ።
እናንተም፦ እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፣ ትእዛዙንስ በመጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ፊት ኀዘንተኞች ሆነን በመሄድ ምን ይረባናል?
ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች! እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ! ልባችሁን አጥሩ።