ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፥ ከወንዝም እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ይገዛል።
ቀኑን ሙሉ ክብርህን ያወራ ዘንድ፣ አፌ በምስጋናህ ተሞልቷል።
አፌን ምስጋና ሞላ ሁልጊዜ ክብርህንና እዘምር ዘንድ።
አንደበቴ በአንተ ምስጋና የተሞላ ነው፤ ስለ ክብርህም ቀኑን ሙሉ እናገራለሁ። ድምፄንም ከፍ አድርጌ ለአንተ ምስጋና አቀርባለሁ።
እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ስሙንም ጥሩ፥ ለአሕዛብም ሥራውን ንገሩ።
እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይሠራታል፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ይሰበስባል።
ለእነርሱ ለራሳቸው ክፉ ነገርን አጸኑ፤ ወጥመድን ይሰውሩ ዘንድ ተማከሩ፤ የሚያምንም የለም ይላሉ።
እርሱ ይኖራል፥ ከዓረብም ወርቅን ይሰጡታል፤ ሁልጊዜም ስለ እርሱ ይጸልያሉ፥ ዘወትርም ይመርቁታል።
ሰማያት የእርሱን ጽድቅ አወሩ፥ አሕዛብም ሁሉ ክብሩን አዩ።