ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፤ በዓልን የሚያደርጉ ሰዎች በምስጋናና በደስታ ቃል ሲያመሰግኑ ተሰሙ።
እኔም፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረት አድርግልኝ፤ አንተን በድያለሁና ነፍሴን ፈውሳት” አልሁ።
ጌታ በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፥ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል።
እኔም “እግዚአብሔር ሆይ! አንተን ስለ በደልኩ ምሕረትን አድርግልኝ፤ ከሕመም ፈውሰኝ” አልኩ።
እልፍኙን በውኃ የሚሠራ፥ ደመናን መሄጃው የሚያደርግ፥ በነፋስ ክንፍም የሚሄድ፥
ለወሰኖችሽም ሰላምን አደረገ፥ የስንዴንም ስብ አጠገበሽ።
እግዚአብሔር ጽድቅንና ምጽዋትን ይወድዳል፤ የእግዚአብሔር ይቅርታው ምድርን ሞላ።
በመከራቸው ጊዜ በማለዳ ወደ እኔ ይገሰግሳሉ፤ እንዲህም ይላሉ፥ “ኑ፤ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፤ እርሱ መትቶናልና፥ እርሱም ይጠግነናል።