አምላኬ፥ አምላኬ፥ ተመልከተኝ፥ ለምን ተውኸኝ? የኀጢአቴ ቃል እኔን ከማዳን የራቀ ነው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ንጉሥ በኀይልህ ደስ ይለዋል፤ በምትሰጠውም ድል እጅግ ሐሤት ያደርጋል።
ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
አምላክ ሆይ! ኀይልን ስለ ሰጠኸው ንጉሥ ደስ ብሎታል፤ ድልን ስለ አቀዳጀኸውም ሐሴት ያደርጋል።
እኔ ግን በእነርሱ ላይ ንጉሥ ሆኜ ተሾምሁ በተቀደሰ ተራራው በጽዮን ላይ።
ፊትህ በተቈጣ ጊዜ እንደ እሳት እቶን አድርጋቸው፤ አቤቱ፥ በቍጣህ አውካቸው፥ እሳትም ትብላቸው።
የእግዚአብሔር ቃል የእሳቱን ነበልባል ይቈርጣል።
ረዳቴ ሆነኽልኛልና፥ በክንፎችህም ጥላ እታመናለሁ።
ስሙ ለዘለዓለም ቡሩክ ነው፥ ከፀሓይም አስቀድሞ ስሙ ነበረ፤ የምድር አሕዛብ ሁሉ በእርሱ ይባረካሉ፥ ሕዝቡ ሁሉ ያመሰግኑታል።
ለእግዚአብሔር አዲስ ምስጋናን አመስግኑ፤ ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑት።
ወደ ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ አመስግኑት፥ ስሙንም አክብሩ፥
የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ፥ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።