በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም ጮኽሁ፤ በቤተ መቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።
አምላክ ሆይ፤ ስለምትመልስልኝ አንተን እጣራለሁ፤ ጆሮህን ወደ እኔ ጣል አድርገህ ጸሎቴን ስማ።
አቤቱ፥ ሰምተኸኛልና ወደ አንተ ጠራሁ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ ቃሌንም ስማ።
አምላክ ሆይ! ልመናዬን ስለምትሰማ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ ቃሌንም ስማ።
ምሕረቱ በእኛ ላይ ጸንታለችና፤ የእግዚአብሔርም እውነት ለዘለዓለም ትኖራለች። ሃሌ ሉያ።
ተቈጡ፥ ነገር ግን አትበድሉ፤ በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ የምታስቡት ይታወቃችሁ።
በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል።
“ምሕረትን ለዘለዓለም አንጻለሁ” ብለሃልና፥ ጽድቅህ በሰማይ ጸና።
አቤቱ፥ ጆሮህን አዘንብልና ስማ፤ አቤቱ፥ ዐይንህን ክፈትና በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ የላከውን የሰናክሬምን ቃል ተመልከት።
እንግዲህ አምላካችን አቤቱ፥ የምድር ነገሥታት ሁሉ አንተ ብቻ እግዚአብሔር እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከእጁ አድነን።”